ቀጥታ፡

በተከሰከሰው አውሮፕላን ላይ መረጃ የማሰባሰብ ስራ እንደቀጠለ ነው

አዲስ አበባ መጋቢት 3/2011 ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ሲበር የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን መረጃ የማሰባሰብ ስራ መቀጠሉን የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

በሚኒስቴሩ የአደጋ ምርመራ ሃላፊ የሆኑት አቶ ሃምድዬ አያሌው ለኢዜአ እንደገለጹት አደጋው በደረሰበት ስፍራ እየተካሄደ ያለው መረጃ የማሰባሰብ ተግባር ላልተወሰነ ጊዜ ይቀጥላል።

የአሜሪካ ብሔራዊ የአየር ትራንስፖርት ደህንነት ቦርድ (ANATBF) እና የቦይንግ ኩባንያ ባለሙያዎች በኢትዮጵያ ከተቋቋመው ኮሚቴ ጋር በመተባበር መረጃ የማሰባሰብ ስራውን እያከናወኑ እንደሆነ ገልጸዋል።

ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነው ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን ከትላንት በስትያ ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው ጊምቢቹ ወረዳ ውስጥ መከስከሱ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም