ቀጥታ፡

የጃፓን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአደጋው የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ

አዲስ አበባ መጋቢት 3/2011 የጃፓን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታሮ ኮኖ በኢትዮጵያ በደረሰው የአውሮፕላን አደጋ በሞቱት ሰዎች የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ።

ከትናንት በስቲያ ከአዲስ አበባ ናይሮቢ ሲበር የመከሰከስ አደጋ ባጋጠመው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን የ157 ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወቃል።

የጃፓን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታሮ ኮኖ በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦችና ዘመዶቻቸው ከልብ የመነጨ መጽናናትን እመኛለሁ ብለዋል።

የአደጋው መንስኤ እስካሁን ያልታወቀ ሲሆን የምርመራ ሂደቱን እንደሚያቀላጥፍ የሚታመንበት መረጃዎችን መዝግቦ የሚይዘው የመረጃ ሳጥን (ብላክ ቦክስ) እና በአውሮፕላኑ ውስጥ ድምጾችን የሚቀርጸው መሣሪያ መገኘቱ ይታወቃል።

በኢቲ 302 አውሮፕላን የመከስከስ አደጋ የ35 አገራት ዜግነት ያላቸው መንገደኞች ህይወት አልፏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም