ቀጥታ፡

የቻይና ፕሬዚዳንት ዥ ፒንግ በአውሮፕላኑ መከስከስ ለደረሰው አደጋ የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ

አዲስ አበባ መጋቢት1 /2011 የቻይና ፕሬዚዳንት ዥ ፒንግ በኢትዮጵያ አውሮፕላን ቦይንግ 737 ማክስ 8 መከስከስ ለደረሰው የህይወት መጥፋት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ።

በተመሳሳይ የቻይና ጠቅላይ ሚኒስትር ሊካ ኬያንግም የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል። መንግስታቸው አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርግም አረጋገጠዋል።

የቻይናው ፕሬዚዳንት ዥ ፒንግ ለፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በላኩት መልዕክት የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል።

በዚህም መሰረት በቻይና ሕዝብና መንግሥት ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለፕሬዚዳንቷ የገለጹት ዥ ፒንግ ለሟች ቤተሰቦች መጽፅናናትን ተመኝተዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥትም ከአደጋው በኋላ የሚሰሩ ሥራዎችን በብቃት እንደሚፈጽመው ያላቸውን እምነት ጠቁመዋል።

በተመሳሳይ የቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊካ ኬያንግም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአውሮፕላኑ መከስከስ ለደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል።

የ157 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው አደጋው የኢትዮጵያዊያና የቻይና ዜግነት ያላቸው ሰዎች መኖራቸውን የጠቆሙት መሪዎቹ ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም