ቀጥታ፡

የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገለጹ

አዲስ አበባ መጋቢት 1/2011 የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ቦይንግ 737 በመከስከሱ በተጓዦችና በበረራ ቡድን አባላት ላይ በደረሰው ህልፈተ ሕይወት የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 የሆነው አውሮፕላን  ዛሬ ማለዳ ከአዲስ አበባ ወደ ኬኒያ ናይሮቢ ሲጓዝ ነው የተከስከስው ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ  ባስተላለፉት መልዕክት በተጓዦችና በበረራ ቡድን አባላት ህልፈተ ህይወት የተሰማቸው ጥልቅ ሃዘን ገልጸው ለሟች ቤተሰቦች እና ወዳጆች መጽናናትን ተመኝተዋል።

ዛሬ ማለዳ 149 መንገደኞችና ስምንት የበረራ ሰራተኞችን ይዞ ወደ ናይሮቢ ሲጓዝ በምሥራቅ ሸዋ ዞን ጊምቢቹ ወረዳ የተከሰከሰው ቦይንግ 737 አውሮፕላን የ33 አገሮችን ዜጎችን አሳፍሮ ሲጓዝ ነበር።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም