ቀጥታ፡

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የአውሮፕላን አደጋው የደረሰበትን ስፍራ ጎበኙ

አዲስ አበባ መጋቢት  1/2011 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የአውሮፕላን መከስከስ አደጋው የደረሰበትን ስፍራ ጎበኙ።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የበረራ ቁጥር ኢቲ 302 የሆነውና ዛሬ ማለዳ ከአዲስ አበባ ወደ ኬኒያ ናይሮቢ ሲጓዝ የተከሰከሰው አውሮፕላን   የወደቀበትን ስፍራ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሰዓታት በፊት ጎብኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሟቾች ከልብ የመነጨ ኀዘናቸውን፤ ለሞቱት ወዳጅ ዘመዶች ደግሞ መጽናናትን ተመኝተዋል።

የአደጋው መንስኤ እንዲጣራ፣ ለሟች ወገኖችም ተገቢው ሁሉ እንዲደረግ መመሪያ ማስተላለፋቸውንም ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ዛሬ ማለዳ 149 መንገደኞችና ስምንት የበረራ ሰራተኞችን ይዞ ወደ ናይሮቢ ሲጓዝ በምሥራቅ ሸዋ ዞን ጊምቢቹ ወረዳ የመከስከስ አደጋ ያጋመጠው ቦይንግ 737 አውሮፕላን የ33 አገራት ዜጎችን አሳፍሮ ሲጓዝ ነበር።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም