ወደ ናይሮቢ ይበር የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመከስከስ አደጋ ገጠመው

155

አዲስ አበባ መጋቢት 1/2011 ከአዲስ አበባ ናይሮቢ ይበር የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 አውሮፕላን የመከስከስ አደጋ ገጠመው።

አውሮፕላኑ ዛሬ ከአዲስ አበባ ተነሥቶ ወደ ኬንያ ናይሮቢ ሲጓዝ ነው ቢሾፍቱ አካባቢ የተከሰከሰው።

149 መንገደኞችን እና ስምንት የበረራ ሰራተኞችን ባሳፈረው አውሮፕላን ላይ ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰ እስካሁን አልታወቀም።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በአደጋው ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ላጡ፣ በኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ስም ኀዘኑን ገልጿል።

የአደጋው መንስኤና የጉዳቱ መጠን እየተጣራ ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቀጣይ ተጨማሪ መረጃዎችን እንደሚያሳውቅ ለኢዜአ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም