ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን የዊልቸር ቅርጫት ኳስ ሳይክልና የቦርድ ድጋፍ ለሶማሌ ክልል ስፖርት ቢሮ ድጋፍ አደረገ

አዲስአበባ የካቲት 30/2011 የኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ለሶማሌ ክልል ስፖርት ቢሮ የዊልቸር ቅርጫት ኳስ ሳይክልና የቦርድ ድጋፍ አደረገ ።

የፌዴሬሽኑ የፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ይመር ሃይሌ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት በክልሉ ስፖርቱን የሚደግፉ አስር ዊልቸርና አንድ የቦርድ ድጋፍ ተደርጓል።

ድጋፍ የተደረገው በስፖርቱ አቅምና ፍላጎት ያላቸው አካል ጉዳተኞችን ተሳታፊ ለማድረግ መሆኑንም ገልጸዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በፌዴራል ደረጃ የዊልቸር ቅርጫት ኳስ አሶሴሽን ለማቋቋም እንደሚረዳም አመልክተዋል።

ከዚህ በፊት የዊልቸር ቅርጫት ኳስ ቦርድ ለአዳማ ከተማ የተሰጠ ሲሆን የዊልቸር ቅርጫት ሳይክሎች ደግሞ ለደቡብ፣ አማራ፣ ኦሮሚያና ትግራይ ክልሎች ድጋፍ መደረጉን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም