ቀጥታ፡

ሴቶች በብሔር መካከል የሚፈጠር ጥላቻን በመከላከል ሚናቸውን እንዲወጡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጠየቁ

አዲስ አበባ የካቲት 29/2011 ሴቶች በብሔር መካከል የሚፈጠር ጥላቻን በመከላከል ሚናቸውን እንዲወጡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጥሪ አቀረቡ።

ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን በአለም ለ108ኛ ፤ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ43ኛ ጊዜ ዛሬ በአፍሪካ ህብረት ተከብሯል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በዚህ ወቅት እንዳሉት ሴቶች በብሔር መካከል የሚፈጠር ጥላቻን በመከላከል በኢትዮጵያ ሰላምና አንድነትን ለማምጣት ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል።

ሴቶች ምሰሶ ተሸካሚዎች መሆናቸውን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ቀጣይ ስራዎቻችሁ የኢትዮጵያን ሰላም፣ አንድነት፣ መፈቃቀርና ይቅርታ እንዲሆን በአንክሮ እንድትሰሩ" ብለዋል።

"የኢትዮጵያ ሴቶችና ሰላም ወዳድ ዜጎች ዝምታ ጥቂቶች እንዲጮሁና ብቻቸውን እንዲደመጡ እያደረገ ነው" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ይህ እንዲሆን ጥቂቶች ድምጻቸውን አሰምተው መጨረሻችንን እንዳያበላሹ በአንድ ልብ እንድትሰሩ" ሲሉ በአደራ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም