ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ በብዙ መከራ የተገነባች በመሆኑ ወደኋላ የሚመልሳት አንዳች ነገር አይኖርም- ጠቅላይ ሚኒስትሩ

አዲስ አበባ የካቲት 29/2011 ኢትዮጵያ ሴቶችን ጨምሮ ብዙዎች የደሙላት፣ የቆሰሉላትና ልጆቻቸውን አጥተው በመከራ የገነቧት አገር በመሆኑ ምንም ኃይል ወደኋላ ሊጎትታት እንደማይችል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናገሩ።

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በአዲስ አበባ ሲከበር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት ንግግር፤ "ኢትዮጵያውያን አረምን በጋራ የማረም አቅም አለን" ሲሉ ጠቅሰው  ነውጥን የሚሹ ጥቂቶች ብቻቸውን እንዳይደመጡ ብዙሃኑ በመተባበር አገሪቱ ከችግሩ የምትሻገርበትን ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባ አሳስበዋል።

"ለትውልድ የማያስቡና የአንድነት ብርታት ያልገባቸው ሰዎች ይዘውን እንዳይጠፉ ለኢትዮጵያ አንድነት በጋራ በመስራት ለችግር ኃላፊነት የሚወስድና ድልን በጋራ የሚጋራ ትውልድ መገንባት ያስፈልጋል" ብለዋል።

ይህንን ለማድረግ ሁሉም ከተባበረ ማንም ምንም ቢሞክር ኢትዮጵያን ሊያስቆማት የሚችል ነገር አይኖርም ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒሰትሩ እንዳሉት በተለይ ሴቶች ውሸትን፣ መግፋትን፣ ማፍረስን፣ ለመግደል መሰለፍን በጋራ በማስቆም ጀግንነታቸውን ለማረጋገጥ በትብብር መንፈስ መስራት አለባቸው።

የዛሬ 43 አመት የሴቶች ቀን መከበር ከመጀመሩ በፊት ሴት እንድትታገል እና ወደ ውጪ እንድትወጣ እድሉ ከተፈጠረባቸው አጋጣሚዎች አንዱ የሁለተኛው አለም ጦርነት ነው ያሉት ዶክተር ዓብይ በወቅቱ  በወንዶች ወደ ውጊያ መዝመት ሳቢያ ኢንደስትሪዎች ሰራተኛ በማጣታቸው ሴቶች 'እንችላለን ቤተሰብና አገር እናስቀጥላለን' ብለው ወንዱ ይሰራ የነበረውን ስራ ሰርተዋል።

ይህም ኢኮኖሚን ፣ የአገር አንድነትን ብሎም ቤተሰብን በማስቀጠል ረገድ ሁነኛ ሚና መጫወት እንደሚችሉ ያረጋገጡበት ጊዜ መሆኑንም አስታውሰዋል። በአሁኑ ወቅትም ሴቶች ይህንን ብቃታቸውን በማሳየት በኢትዮጵያ ሰላምንና አንድነትን ለማምጣት ሚናቸውን ሊወጡ እንደሚገባ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም