የእጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ይደረጋሉ - ኢዜአ አማርኛ
የእጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ የፊታችን ቅዳሜና እሁድ ይደረጋሉ
አዲስ አበባ የካቲት 28/2011 የኢትዮጵያ የእጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ የስምንተኛ ሳምንት ጨዋታዎች የፊታችና ቅዳሜና እሁድ ይደረጋሉ።
ቅዳሜ የካቲት 30 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ትንሿ ሁለገብ ስታዲየም ሁለት ጨዋታዎች ይካሄዳሉ።
በዚህም መሰረት ፌደራል ፖሊስ ከድሬዳዋ ከተማ ከጠዋቱ ሶስት ሰዓት ፌደራል ማረሚያ ቤቶች ከቡታጅራ ከተማ ከረፋዱ 4 ሰአት ከ30 ደቂቃ ላይ ጨዋታቸውን ያካሂዳሉ።
እሁድ መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም ዱራሜ ላይ ከምባታ ዱራሜ ከጎንደር ከተማ፤ መቐለ ላይ መቐለ ሰብዓ እንደርታ ከአምናው የሊጉ አሸናፊ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጋር በተመሳሳይ ከጠዋቱ ሶስት ሰአት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
በስምንተኛ ሳምንት የሊጉ መርሃ ግብር የሊጉ መሪ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማና መከላለያ ጨዋታ የማያደርጉ አራፊ ክለቦች ናቸው።
በእጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ 10 ክለቦች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በሌላ በኩል በኢትዮጵያ ወንዶች ቅርጫት ኳስ ፕሪሚየር ሊግ በምድብ አንድና ሁለት የሚገኙ ክለቦች ከነገ ጀምሮ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
በምድብ አንድ ነገ አዳማ ከተማ ከሀዋሳ ከተማ ቅዳሜ የካቲት 30 ቀን 2011 ዓ.ም አዳማ ከተማ ከኢትዮጵያ ውሃ ስፖርት እሁድ መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም ሀዋሳ ከተማ ከኢትዮጵያ ውሃ ስፖርት በተመሳሳይ ከጠዋቱ ሶስት ሰአት አዳማ ላይ ይገጥማሉ።
በምድብ ሁለት ነገ በአዲስ አበባ ትንሿ ሁለገብ ስታዲየም የካ ክፍለ ከተማ ከወልቂጤ ከተማ ከረፋዱ 4 ከ 30 ደቂቃ ላይ ይጫወታሉ።
በምድቡ ቅዳሜ የካቲት 30 ቀን 2011 ዓ.ም ከረፋዱ 4 ሰአት ከ30 ደቂቃ በራስ ሃይሉ ስፖርት ማዕከል ጎንደር ከተማ ከየካ ክፍለ ከተማ እሁድ መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ትንሿ ሁለገብ ስታዲየም ወልቂጤ ከተማ ከጎንደር ከተማ ከጠዋቱ ሶስት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ሴቶች ቅርጫት ኳስ ፕሪሚየር ሊግ የምድብ ሁለት ጨዋታዎች ከነገ ጀምሮ ይካሄዳሉ።
ነገ በአዲስ አበባ ትንሿ ሁለገብ ስታዲየም ፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ከሀዋሳ ከተማ፤ ቅዳሜ የካቲት 30 ቀን 2011 ዓ.ም ደግሞ በራስ ሃይሉ ስፖርት ማዕከል ጎንደር ከተማ ከፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በተመሳሳይ ሶስት ሰአት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
እሁድ መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም በዛው ምድብ ሁለት በአዲስ አበባ ትንሿ ሁለገብ ስታዲየም ሀዋሳ ከተማ ከጎንደር ከተማ ጠዋት ሶስት ሰአት ይጫወታሉ።
በኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን አዲስ የውድድር ፎርማት መሰረት በወንዶችና በሴቶች በተመሳሳይ በምድብ ሁለት እንዲሁም በወንዶች በምድብ አንድ የሚገኙ ክለቦች በቅደም ተከተል ወደ አዲስ አበባና አዳማ በማቅናት ለሶስት ተከታታይ ቀናት እርስ በእርስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
በፕሪሚየር ሊጉ በሁለቱም ጾታዎች በተመሳሳይ ስድስት ቡድኖች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በተጨማሪም እሁድ መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም ሐበሻ ሲሚንቶ የወንዶች ቮሊቮል ፕሪሚየር ሊግ በአዲስ አበባ ትንሿ ሁለገብ ስታዲየም ፌደራል ማረሚያ ቤቶች ከወላይታ ድቻ ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ ተስተካካይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
መጋቢት 3 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ትንሿ ሁለገብ ስታዲየም መከላከያ ከወላይታ ድቻ ከጠዋቱ ሶስት ሰአት ተስተካካይ ጨዋታቸውን ካደረጉ በኋላ የቮሊቦል ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር እንደሚጠናቀቅ የኢትዮጵያ ቮሊቦል ፌዴሬሽን አስታውቋል።
በሐበሻ ሲሚንቶ የወንዶች ቮሊቮል ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች እየተሳተፉ ይገኛሉ።