በደቡብ ክልል የፀጥታ ችግሮች ላይ የኃይማኖት መሪዎች በአርባ ምንጭ እየመከሩ ነው

120

አርባ ምንጭ የካቲት 27/2011 የደቡብ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ በወቅታዊ የፀጥታ ችግሮች ዙሪያ ከኃይማኖት መሪዎች ጋር በአርባ ምንጭ ከተማ እየመከረ ነው ፡፡

ምክክሩ በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች በኃይማኖት ሽፋን ለሚፈጠሩ የፀጥታ ችግሮች የመፍትሄ አቅጣጫዎች እንደሚያስቀምጥ የቢሮው ኃላፊ አቶ ወንድሙ ገብሬ ገልጸዋል ፡፡

መድረኩ ቤተ እምነቶች ሰላምን በማረጋገጥ ብሎም  በልማትና  በዴሞክራሲ ግንባታ ጉዳዮች ላይ ይነጋገራል ብለዋል ፡፡

በተጨማሪም የኃይማኖት አባቶችና የመንግሥት መሪዎች  ተቀናጅተው ለመሥራት እንደሚያስችላቸው አቶ ወንድሙ አስታውቀዋል።

በቢሮው የብዙሃን ሙያ ማህበራትና የሃይማኖትና እምነት ጉዳዮች አያያዝ ዘርፍ ባለሙያ አቶ እውነት አራጌ እንደገለጹት ለውጡን ተከትሎ በሃይማኖት፣በድንበር፣ በማንነትና ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍልን ተመርኩዘው ግጭቶች ተከስተዋል፡፡

ሃላባ፣ ስልጤ ፣ ጉራጌ፣ ጋሞ ፣ ጎፋና የም  የጸጥታ ችግሮች የተከሰባቸው አካባቢዎች እንደነበሩ ገልጸዋል፡፡

ግጭት በውይይትና በሕግ አግባብ ካልተፈታ ሰብዓዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውሶች እንደሚያስከትል ጠቁመዋል፡፡

የክልሉ ሕዝብ ተከባብሮ ተቻችሎ የሚኖርበት እሴት ዳግም እንዲያንሰራራ መንግሥትና የሃይማኖች መሪዎች ትውልድን በመቅረጽ ድርሻቸውን እንዲወጡ ባለሙያው አመልክተዋል፡፡

ለሁለት ቀናት በሚቆየው መድረክ ከክልሉ ሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች የተውጣጡ ከ400 በላይ የእምነት መሪዎች በመሳተፍ  ላይ ናቸው፡፡

በክልሉ አገራዊውን ለውጥ ተከትሎ በተከሰቱት የጸጥታ ችግሮች  በሕይወትና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወቃል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም