ጠቅላይ ሚኒስትር አብይና የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጁባ ገብተዋል - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይና የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጁባ ገብተዋል
የካቲት 25/2011 ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ደቡብ ሱዳን መዲና ጁባ ግብተዋል፡፡
ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ጁባ አለም አቀፍ የአየር ማረፊያ ሲደርሱ ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪርና የደቡብ ሱዳን ከፍተኛ ባለስልጣናት ሞቅ ያለ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡
መሪዎቹ በቆይታቸው በቀጣናዊ ሰላም፣በኢኮኖሚ ትስስር፣እና በመሰረተልማት እንዲሁም በቅንጅት ለመስራት የሚያስችሏቸው ጉዳዮች ላይም ከደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንትና ከከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ይመክራሉ ተብሏል፡፡
ኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ወገኖችን ለማቀራረብና ሰላም ለማምጣት ጠንካራ ተሳትፎ ስታደርግ ቆይታለች፡፡
ይፋዊ ጉብኘቱ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አነሳሽነት በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና የኢኮኖሚና የፖለቲካ ትብብር ለመፍጠር የታለመውን ግብ ለማሳካት የተካሄደ ነውም ተብሏል፡፡
የደቡብ ሱዳን የኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር ሚካኤል ማኩዬ ትናንት በሰጡት መግለጫ እንዳሉት የጉብኝቱ አላማ የኢትዮጵያ፣የደቡብ ሱዳን እና የኤርትራን ግንኙነት ማጠናከር ነው፡፡
መሪዎቹ ከፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ጋር የሶስትዮሽ እና የተናጥል ውይይት ያደርጋሉ፡፡