ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ከኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር አስመራ ገቡ

አዲስ አበባ የካቲት 24/2011 ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ሰሞኑን በኢትዮጵያ ቆይታ ካደረጉት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር ለጉብኝት ዛሬ ኤርትራ አስመራ ገብተዋል።

ሁለቱ መሪዎች አስመራ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የሶስቱ ጎረቤት አገራት መሪዎች በተለይም በአፍሪካ ቀንድ የኢኮኖሚ ውህደትን ለማምጣት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ እንደሚመክሩ ይጠበቃል።

መሪዎቹ በቀጠናው በሚስተዋሉ ወቅታዊ ጉዳች ዙሪያም ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም