ቀጥታ፡

አሜሪካ የኦሳማ ቢላደን ልጅ ያለበትን ለሚጠቁማት 1 ሚሊየን ዶላር ሽልማት አዘጋጀች

የካቲት 22/2011 የአሜሪካ መንግሥት የቀድሞ የአል ቃኢዳ መሪ የኦሳማ ቢላደን ልጅ ሀምዛ ቢላደን ያለበትን ለሚጠቁማት 1 ሚሊየን ዶላር ሽልማት አዘጋጀች፡፡

ቢቢሲ እንደዘገበው ሀምዛ ቢን ላደን የአል ቃኢዳ ታጣቂ ቡድን መሪ ለመሆን በመዘጋጀት ላይ እንደሆነም ተነግሯል።

የኦሳማ ቢን ላደን ልጅ በአሁኑ ሰዓት በአፍጋኒስታንና በፓኪስታን ድንበር አቅራቢያ ሊኖር ይችላል የሚል ግምት መኖሩን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።

አሜሪካ እድሜው 30 ዓመት እንደሆነ የሚገመተውን ሀምዛ ቢን ላደን ከሁለት ዓመት በፊት በዓለም አቀፋዊ አሸባሪነት ፈርጃዋለች።

ከጥቂት ዓመታት በፊት በድምፅና በምስል በለቀቀው መልዕክት አሜሪካና ምዕራባዊ አጋሮቿ ላይ ጥቃት በመፈጸም የአባቱን ሞት እንዲበቀሉ ለተካታዮቹ ጥሪ አስተላልፏል።

በፈረንጆቹ 2011 የአሜሪካ ልዩ ኃይሎች ፓኪስታን አቦታባድ በሚገኘው የራሱ ግቢ ኦሳማ ቢን ላደንን መግደላቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም