7 ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ግንባር በመፍጠር በጋራ ለመስራት ተስማሙ - ኢዜአ አማርኛ
7 ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ግንባር በመፍጠር በጋራ ለመስራት ተስማሙ
አዲስ አበባ የካቲት 20/2011 በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ 7 ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ግንባር በመፍጠር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ።
በጥምረት ለመስራት የተስማሙት የመላዉ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ)፣ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ)፣ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ህብርት( ኢዴህ)፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት (ኢብአ)፣ የአፋር ህዝቦች ፍትሀዊይ (አህፍ)፣ የአፋር ህዝቦች ነፃነት ፓርት እና የኦሮሞ ህዝብ ፍትሃዊ ፓርቲ ናቸው።
ፓርቲዎቹ ተጣምረው በግንባር አብሮ ለመስራት እንዲቻላቸው የተዘጋጀው የስምምነት ሰነድ ዛሬ ሲፈረም እንደተገለፀው የፖለቲካ ማህበራቱ በጥምረት ለመስራት መወሰናቸው የሚታገሉለትን ዓላማ ከግብ ለማድረስ ያስችላቸዋል።
ከዚሀም ሌላ ወቅቱ የሚጠይቀውን የፖለቲካ ተግባር በአግባቡ ለመፈፀምም አቅም እንደሚሆናቸው ፓርቲዎቹ ተናግረዋል።
ጥምረቱ አሁን የተጀመረው የፖለቲካዊ ለውጥ እንዲቀጥል፤ በተለይም በአገሪቱ ሰላምና የህግ የበላይነትን ለማጠናከር፣ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ የሚካሄድበትን ሁኔታ ለማመቻቸት በአጠቃላይ ጠንካራ ተቋማዊ የሆነ ዴሞክራሲ ለመገንባት ትልቅ ሚና እንዳለውም ተመልክቷል።
በአገሪቱ በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተለያየ መንገድ ተቋቁመው ተግባራቸውን በተበታትነ መንገድ ለማካሄድ የተገደዱት ባለፉት ዓመታት በነበረው ፖለቲካዊ ተፅእኖ እንደሆነም የፓርቲዎቹ ሊቃነመናብርት ገልፀዋል።
ከዚህም ሌላ ወቅቱ የሚጠይቀውን የፖለቲካ ተግባር በአግባቡ ለመፈፀምም አቅም እንደሚሆናቸው በጋራ መግለጫቸው አሳውቀዋል።
ስምምነቱ ጠንካራ ፓርቲን በመፍጠር አሁን የተጀመረው የፖለቲካዊ ለውጥ እንዲቀጥል፤ በተለይም በአገሪቱ ሰላምና የህግ የበላይነትን ለማጠናከር፣ ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ የሚካሄድበትን ሁኔታ ለማመቻቸት በአጠቃላይ ጠንካራ ተቋማዊ የሆነ ዴሞክራሲ ለመገንባት ትልቅ እድል ይፈጥራልም ተብሏል።
በብዝሃነት፣ እኩልነትና አንድነት ላይ የተመሰረተች ኢትዮጵያን ለመፍጠር ያለመ ጥምረት በመሆኑ ወደፊትም አብሮ ለመስራት የሚፈልግ ማንኛውም ፓርቲ በማንኛውም ወቅት ወደ ጥምረቱ መቀላቀል እንደሚችልም ፓርቲዎቹ ጥሪ አቅርበዋል።
በአገሪቱ በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተለያየ መንገድ ተቋቁመው ተግባራቸውን በተበታትነ መንገድ ለማካሄድ የተገደዱት ባለፉት ዓመታት በነበረው ፖለቲካዊ ተፅእኖ እንደሆነም የፓርቲዎቹ ሊቃነመናብርት ገልፀዋል።
በአሁኑ ወቅት ወቅት 24 አገራዊና 42 ክልላዊ ተፎካካሪ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና ተሰጥቷቸው በመንቀሳስ ላይ የሚገኙ ሲሆን ፖለቲካዊ ለውጡን ተከትሎ በርካታ ፓርቲዎች በጥምረትና ግንባር ለመፍጠር እየተንቀሳቀሱ ነው።