ቀጥታ፡

ጅማ አባ ጅፋር በሜዳው ነጥብ ጣለ

ጅማ የካቲት 17/2011 በኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ዛሬ ፋሲል ከተማን በሜዳው ያስተናገደው ጅማ አባ ጅፋር ነጥብ ጥሏል።

ጅማ አባ ጅፋር ነጥቡን የጣለው ከተጋጣሚው ጋር ባዶ ለባዶ በመውጣቱ ነው።

የሊጉ የዓመቱ መጀመሪያ ዙር መጨረሻ ግጥሚያ የተገናኙት ክለቦቹ ጅማ አባ ጅፋር የመሃል ሜዳ ጨዋታ ብልጫ ቢወሰድበትም፤ድንቅ የግብ ሙከራዎች ያደረገባቸው አጋጣሚዎች ነበሩ።

የዛሬውን ጨዋታ ተከትሎ ጅማ አባ ጅፋር በ21 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ይዟል።

ፋሲል ከተማ ደግሞ 25 ነጥብ በመሰብሰብ ደረጃውን አራተኛ አድርጓል።

ጅማ አባ ጅፋር የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ የ2010 ሻምፒዮን ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም