አሶሳ ዘጠነኛውን የከተሞች ፎረም ለማስተናገድ ተመረጠች

355

ጅግጅጋ  የካቲት 14/2011 የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ዘጠነኛውን የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም እንድታስተናግድ ተመረጠች።

ስምንተኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም 'መደመር ለኢትዮጵያ ከተሞች ብልፅግና' በሚል መሪ ሃሳብ በሱማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ከየካቲት 9 እስከ 14 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ ተካሂዷል።

ዘጠነኛውን የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም ለማስተናገድ ከሰባት ክልሎች ከቀረቡ 12 ከተሞች ውስጥ የአሶሳ ከተማ የቀረበውን የውድድር መስፈርት በማሟላት ተመርጣለች።

የውድድሩ መስፈርት የከተማ በቂ የሰነድ ዝግጅት፣ ፍትሃዊነት፣ ወቅታዊ ሁኔታ፣ ታዳሚዎችን የማስተናገድ አቅምና መስህብ እንዲሁም የመሠረተ ልማት ዝርጋታዎች ናቸው።

አሶሳ ከተማ የተመረጠችው በውድድሩ የመጨረሻ ዙር የደረሱት ወላይታ ሶዶና ጅማ ከተሞችን በማሸነፍ ነው።  

በስምንተኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም ሀዋሳ ከተማ አንደኛ ሆና አሸንፋለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም