ቀጥታ፡

82 ኛው የሰማእታት ቀን ታስቦ ውሏል

የካቲት 12/2011- 82 ኛው የሰማእታት ቀን አዲስ አበባ በሚገኘው የ6 ኪሎ የሰማእታት  ሃውልት  በዛሬው እለት ታስቧል፡፡

የካቲት 12 ፋሺሽት ጣሊያን 30 ሺህ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን በግፍ የጨፈጨፈበትን እለት ለመዘከር የሚታወስ ቀን ነው፡፡  

አርበኞቹ አብርሃም ደቦጭና ሞገስ አስገዶም ወራሪው የጣልያን ጦር መኮንን በሆነው ግራዚያኒ ላይ ላደረጉት የግድያ ሙከራ ጭፍጨፋው የበቀል ምላሽ ነው ፡፡

የጣልያን ወራሪ በሶስት ቀናት ውስጥ ህፃን አዋቂ ሳይል ያለምንም ልዩነት 30 ሺህ ዜጎችን ጨፍጭፏል፣ 1ሺህ 469 ሰዎችም በቀጣዩ ወር ተገለዋል፤ ከአንድ ሺህ በላይ ኢትዮጵያውንም ታስረው ከአገር እንዲወጡ ሆኗል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ተወካይና የኢትዮጵያ አርበኞች ማህበር ቀኑን  ለመዘከር በሰማእታት  ሀውልት  ስር የአበባ ጉንጉን አኑረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም