ቀጥታ፡

ጅማ አባጅፋር ተጋጣሚውን አሸነፈ

ጅማ የካቲት 9/2011 በስድስተኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ  ዛሬ በተካሄደው ተስተካካይ የእግር ኳስ ጨዋታ ጅማ አባጅፋር ደደቢትን አንድ ለባዶ በሆነ ውጤት አሸነፈ

ለጅማ አባጅፋር የማሸነፊዋን ጎል ያስቆጠረው ተስፋዬ መላኩ በ55ኛ ደቂቃ ላይ በማአዘን ምት የተሻገረችለትን ኳስ በቅንጭላት በመግጨት ነው፡፡

የደደቢት ክለብ  አልፎ አልፎ  ወደ ተቃራኒ ጎል ክልል በመድረስ የሚሞክሯቸው ኳሶች ጥንካሬን ያሳየ ቢሆንም ኢላማቸውን የጠበቁ አልነበሩም፡፡

ጅማ አባጅፋር ባለፈው ሳምንት   ወደ ሀዋሳ አቅንቶ በደቡብ ፖሊስ ያልተጠበ የስድስት ለአንድ  ሽንፈት ደርሶበት መመለሱ ይታወሳል፡፡

ዛሬ በሜዳው ማሸነፉን ተከትሎ ደረጃውን ከ13ኛ ወደ 10ኛ ደረጃ ያደረሰው ሲሆን በቀጣይ ሶስት ተስተካካይ ጨዋታዎች እንደሚኖሩት ታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም