ቀጥታ፡

የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን አዲስ አበባ ገባ

አዲስ አበባ  የካቲት 7/2011 የኤርትራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲና የባህል ልዑክ አዲስ አበባ ገባ።

55 አባላትን የያዘው ልዑክ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች አቀባበል አድርገውለታል።

ልዑኩ በኢትዮጵያ በሚኖረው ቆይታ በአዲስ አበባና በተለያዩ ክልሎች የሁለቱን አገራት ትስስር የሚያጎለብቱ የኪነ-ጥበብ ሥራዎችን እንደሚያቀርብ ይጠበቃል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ እንዳመለከተው ከሆነ ልዑኩ ከኢትዮጵያ የባህል ቡድን ጋር በመሆን የካቲት 9 በባህዳር፣ የካቲት 10 በአዳማ እና የካቲት 12 በሀዋሳ የሙዚቃ ዝግጅቶቹን ያቀርባል።  

የካቲት 14 ቀን 2011 ዓ.ም ደግሞ 25 ሺህ የሚጠጋ ህዝብ የሚያሳትፍ የማጠቃለያ መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚካሄድ ለማወቅ ተችሏል። ከአንድ ወር በኋላም የኢትዮጵያ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ቡድን በኤርትራ ተመሳሳይ ቆይታ እንደሚያደርግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም