የኤሌክትሪክ መቆራረጥና ከፍተኛ የኃይል ስርጭት በንብረት ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው - ተጠቃሚዎች - ኢዜአ አማርኛ
የኤሌክትሪክ መቆራረጥና ከፍተኛ የኃይል ስርጭት በንብረት ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው - ተጠቃሚዎች
አዲስ አበባ የካቲት 7/2011የኤሌክትሪክ መቆራረጥና ከፍተኛ የኃይል ስርጭት በንብረት ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ለኪሳራ እየዳረጋቸው መሆኑን ተጠቃሚዎች ገለጹ።
አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡት ተጠቃሚዎች የተቋሙ አሰራር ውጣ ውረድ የበዛበት በመሆኑ ለኪሳራ መዳረጋቸውን ነው የተናገሩት።
የክሊን ላውንደሪ ሶሉሽን የልብስ ንፅህና አገልግሎት ባለቤትና ስራ አስኪያጅ አቶ በፍቃዱ አዳነ እንደሚሉት የኤሌክትሪክ ኃይል ለቀናት መቋረጥና ከፍተኛ የኃይል ስርጭት በንብረታቸው ላይ ጉዳት በማድረሱ በስራቸው ላይ እንቅፋት ፈጥሯል።
በተደጋጋሚ ጊዜ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጦ ሲመጣ ከፍተኛ ኃይል ስለሚኖር የልብስ ማጠቢያ ማሽን የኃይል መቆጣጠሪያ /ፊዮዝ/ ይቃጠላል ይህም ለወጪ ይዳርገናል ብለዋል፡፡
ሌላዋ አስተያየት ሰጪ የዝናብ ወዛእምና ጓደኞቻቸው የደረቅ ምግብ ህብረት ሽርክና ማህበር አባል ወይዘሮ ወዛእም ገብረስላሴም የኤሌክትሪክ ኃይል ማነስ በማሽን ላይ በሚደርሰው ጉዳት ማህበራቸው ለሦስት ወራት ያለ ስራ ማቋረጡን ገልጸዋል።
አቶ በፍቃዱ አዳነ፡-
ተቋርጧል የአካባቢው ሰው ካልሆነ በቀር አሁን ትስስር የለንም ሶስት ወር ያህል ማሽን ተቃጥሎ መግዣ ብርም ስላልነበረን በዛ ሠዓት ገዝተን ማቅረብ አልቻልንም።'' መውጫ 3፡06
በንብረት ላይ ስለደረሰው ጉዳት በአቅራቢያቸው ለሚገኝ የኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ቢያሳውቁም መፍትሄ እንዳላገኙ አቶ በፍቃዱ ገልጸዋል።
በኤሌክትሪክ ኃይል ለሚደርሰው ጉዳት ኀብረተሰቡ ምን ሲያሟላ የካሳ ክፍያ እንደሚከፈለውና ምን አይነት ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት ማስገንዘብ እንዳለበትም ተናግረዋል።
ጥያቄያችንን በተደጋጋሚ ለሚመለከተው አካል ብናቀርብም ሰሚ አጥተናል ሲሉ ቅሬታቸውን ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በበኩሉ ከደንበኞቹ የሚቀርበውን ቅሬታ ተከትሎ የጉዳቱ ሁኔታ በተቋሙ ባለሙያዎች ከተረጋገጠ የካሳ ክፍያ እንደሚፈጸም ገልጿል።
በአገልግሎቱ የአካባቢ፣ ማህበራዊ ጤናና ሙያ ላይ ደህንነት ዳይሬክተር አቶ ኪሮስ ሐዱሽ እንዳሉት በኃይል መቆራረጥ፣ በከፍተኛ የኃይል ስርጭትና በኃይል ማነስ በሰውና በንብረት ላይ ለደረሰው አደጋ አገልግሎቱ በኢንሹራንስ ፖሊሲና መመሪያ መሰረት ተገቢውን ክፍያ እየተፈጸመ ነው።
የካሳ ክፍያውን ለመፈፀም ኀብረተሰቡ በአደጋው ጉዳት ለደረሰበት ንብረት የባለቤትነት ማረጋገጫ ይዞ መቅረብና አደጋው በተቋሙ ችግር የተፈጠረ ስለመሆኑ በቴክኒክ ምርመራ መረጋገጥ እንዳለበትም ዳይሬክተሩ አስረድተዋል።
አገልግሎቱ በኤሌክትሪክ ኃይል ስለሚደርሰው ጉዳትና ካሳ አከፋፈል በመገናኛ ብዙኃንና በማህበራዊ ሚዲያ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እየሰራ ቢሆንም የተጠናከረ ለማድረግ በየቅርንጫፎቹ የኮሙኒኬሽንና የደህንነት አደረጃጀት ማዋቀሩን ጠቁመዋል።
በተያዘው በጀት ዓመት አጋማሽ በኤሌክትሪክ ኃይል በደረሰ አደጋ የተቋሙን ሠራተኞች ጨምሮ ለአራት ሰዎች የህይወት፣ ለ108 የንብረት ካሳ መፈጸሙንም አቶ ኪሮስ ገልጸዋል።