7ኛው የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ቀንን አስመልከቶ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው

106

አዳማ የካቲት 6/2011 ሰባተኛው የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት  ቀን  ምክንያት በማድረግ በአዳማ ከተማ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው

በዓሉ " ህገ መንግስታዊ ታማኝነታችንና ህዝባዊ ባህሪያችን ጠብቀን የተጀመረው ሀገራዊ ለውጥ እናስቀጥላለን " በሚል መሪ ሃሳብ በሀገር  አቀፍ ደረጃ ነገ ይከበራል

በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲዮም የሚከበረው ይሄው ሰባተኛው የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ቀን ምክንያት በማድረግ እየተካሄደ ያለው ውይይት የተመራው በኦሮሚያ ክልል ፕሬዝደንት አቶ ለማ መገርሳ ነው፡፡

በፓናል ውይይቱ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ሰዓረ መኮንን መከላከያ በለው ሂደት ውስጥ የሚል የመነሻ ፅሁፍ አቅርበዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ታሪካዊ ጉዞ ከትናንት እስከ ዛሬ የሚል የመነሻ ፅሁፍ ደግሞ በአየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ብርጋዴል ጀነራል ይልማ መርዳሳ ቀርቧል፡፡

በውይይት መድረኩ የመከላከያ ሚኒስትሯ ወይዘሮ አይሻ መሐመድ፣ አባገዳዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አርበኞች፡ ሚነስትሮች፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎች፣  የአዳማና አከባቢዋ ነዋሪዎች ተገኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም