የፊፋ ክፍለ አህጉራዊ ቢሮ ዛሬ በአዲስ አበባ ተከፈተ - ኢዜአ አማርኛ
የፊፋ ክፍለ አህጉራዊ ቢሮ ዛሬ በአዲስ አበባ ተከፈተ
አዲስ አበባ የካቲት 4/2011 ማህበሩ ለምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ እግር ኳስ የሚውለውን ክፍለ አህጉራዊ ቢሮ ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ አስመርቁዋል።
የፊፋው ፕሬዝዳንት ጂያን ኢንፋንቲኖ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጅራ፣ የስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ርስቱ ይርዳ፣ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትሩዋ ዶክተር ሂሩት ካሳው እንዲሁም የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን አባል ሃገራት ተወካዮች በተገኙበት ቢሮው ተመርቆ ተከፍቷል።
በአዲስ አበባ ስራውን የጀመረው የፊፋ ክፍለ አህጉራዊ የልማት ቢሮ ከዚህ ቀደም በሴኔጋልና በደቡብ አፍሪካ የተከፈተ ሲሆን አሁን ለሶስተኛ ጊዜ በአዲስ አበባ መከፈቱ እንደሆነም ተገልጿል።
የቢሮው መከፈት ለአጠቃላይ እግር ኳስ እድገቱና መሰል ጉዳዮች አገሪቷን በቅርበት እንደሚረዳም እንዲሁ።