የኢትዮጵያ ሴቶች የቮሊቦል ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ ተካሂደዋል

56
አዲስ አበባ  ግንቦት 20/2010 በ2010 ዓም የኢትዮጵያ ሴቶች የቮሊቦል ፕሪሜርሊግ ዛሬ በተካሄደው ጨዋታ ኢትዮጵያ ውሃ ስራዎችና ጌታ ዘሩ ስፖርት ክለብ አሸናፊ ሆነዋል። በአዲስ አበባ ትንሿ ስታዲየም በተደረገ ጨዋታ ጌታ ዘሩ ስፖርት ክለብ የኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት አካዳሚን በሶስት የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 3ለ0 በሆነ ውጤት መርታት ችሏል። በሌላ ጨዋታ ውሃ ስራዎች ፌዴራል ማረሚያ ቤቶችን በሶስት የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 3ለ0 በሆነ ውጤት መርታት ችሏል። የኢትዮጵያ ሴቶች ቮሊቮል ፕሪሚየር ሊግ የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታዎች ግንቦት 25 እና ሰኔ 3 ቀን 2010 ዓ ም የሚደረጉ ይሆናል። የሊጉን የደረጃ ሰንጠረዥ የውሃ ስራዎችና የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች በተመሳሳይ አስራ ሁለት ነጥብ ባሸነፏቸው የጨዋታ መጠን ተለያይተው አንደኛና ሁለተኛ ደረጃን ይዘዋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም