የህወሓት 44ኛ ዓመት ምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ የ10 ኪሎ ሜትር ሩጫ ይደረጋል

64

መቀሌ ጥር 30/2011 የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ(ህወሓት) 44ኛ ዓመት ምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ የ10 ኪሎ ሜትር ሩጫ በ12 የክልሉ ከተሞች ይካሄዳል ተባለ።

በከተሞቹ ውድድሩ የሚካሄደው ''የሰማዕታትን አደራ ተቀብለን ድህነትና ኋላቀርነት ለማሰወገድ አንድነታችን አጠናክረን እንረባረባለን!'' በሚል መሪ ቃል ነው።

የውድድሩ አስተባባሪ አቶ ሶፊናስ ከበደ ዛሬ ውድድሩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ውድድሩን ያዘጋጁት የህወሓት ጽህፈት ቤትና የትግራይ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ቢሮ ትብብር ነው።

የካቲት 10/2011 በሚካሄደው ውድድር ከ70 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ የደርግ መንግሥትን ለመጣል የትጥቅ ትግል የጀመረው የካቲት 11 ቀን 1967 ነበር።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም