ቀጥታ፡

የሶማሌ ክልል የ12 ምክር ቤት አባላቱን ያለመከሰስ መብት አነሳ

ጅግጅጋ ጥር 30/2011 የሶማሌ ክልል ምክር ቤት በሰብዓዊ መበት ጥሰትና በሙስና ወንጀሎች የተጠረጠሩ የ12 የምክር ቤት  አባላቱን ያለመከሰስ መብት አነሳ።

ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ ያለመከሰስ መብታቸው ከተነሱት መካልል የቀድሞው የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባዔና የኢትዮጵያ ሶማሌ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(ኢሶሕዴፓ) ሊቀመንበር የነበሩት አቶ መሐመድ ረሺድ ይገኙበታል።

እንዲሁም የቀድሞዋ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሱዓድ አህመድና የቀድሞዋ ክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ማጂዳ መሐሙድም ያለመከከሰስ መብታቸው ተነስቷል።

የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሐመድ ዑመርና የ47 የክልሉ መንግሥት ባለሥልጣናትና ግለሰቦች ጉዳይ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመታየት ላይ መሆኑ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም