በደቡብ ክልል በ450ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ይካሄዳል

70

ሐዋሳ ጥር 23/2011 በደቡብ ክልል በ450ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የተቀናጀ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ለማካሄድ ዝግጅት ማድረጉን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ አስታወቀ።

በመጪው ሳምንት ለሚጀመረው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ሕዝባዊ ተሳትፎን ለማጠናከር ዓላማ ያደረገ መድረክ በሐዋሳ ተካሂዷል ።

የቢሮው ኃላፊው አቶ ጥላሁን ከበደ በወቅቱ እንደገለጹት ዘንድሮ የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራውን ለማስጀመር 3ሺህ 760 ንዑስ ተፋሰሶች ተለይተዋል።

"ሥራው የአካባቢን ተጨባጭ ሁኔታና ጥራትን መሰረት አድርጎ እንዲካሄድ ትኩረት ተሰጥቷል" ብለዋል ።

በደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት የገጠር ፖለቲካና አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ወልደሚካኤል በበኩላቸው ለአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራው የሕዝብ ተሳትፎ የማጠናከር ሥራው በክልሉ በተዘረጉ አደረጃጀቶች የሚመራና የሚታገዝ መሆኑን ተናግረዋል።

በክልሉ ከ2003 ጀምሮ በተከናወኑ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራዎች ያጋጠሙ ጠንካራ ተሞክሮዎችና ተግዳሮቶች ተለይተው የጋራ አቅጣጫ መያዙ ታውቋል ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም