አስተዳደሩ ለወሳኝ ኩነትና ለሌሎችም የሚሰጣቸውን የምስክር ወረቀቶች ወደ ዲጂታል ሊቀይር ነው

92

አዲስ አበባ ጥር 21/2011 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሳኝ ኩነቶች፣ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ካርታና የስምንተኛ ክፍል መልቀቂያ የምስክር ወረቀትን ወደ ዲጂታል አሰራር ሊቀይር መሆኑን አስታወቀ።

ከአዲስ አበባ ከንቲባ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ስራውን ለማከናወን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና ትሮይ ሴኪዩሪቲ ግሩፕ የተሰኘ የአሜሪካ ኩባንያ ስምምነት ፈጽመዋል።

የትምህርት ማስረጃዎችን በተለይም የስምንተኛ ክፍል ውጤት የምስክር ወረቀት፣ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ፣ የልደት፣ ሞትና የጋብቻ የምስክር ወረቀቶችን በዘመናዊ ለመቀየር ተስማምተዋል።

በከተማዋ የሚስተዋለውን ህገ-ወጥና ሃሰተኛ መታወቂያ ለማስቀረትም የከተማ አስተዳደሩ የነዋሪ መታወቂያን በዲጂታል እየቀየረ መሆኑን ገልጿል።

የከተማዋ ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ መረጃዎቹን ወደ ዲጂታል መለወጥ ህገ-ወጥ ማስረጃን ከማስቀረቱ ባሻገር የሚሰጠውን አገልግሎትም ቀልጣፋና ዘመናዊ እንደሚያደርገው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም