አየር መንገዱ በ1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ያስገነባው ስካይ ላይት ሆቴል ተመረቀ - ኢዜአ አማርኛ
አየር መንገዱ በ1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ያስገነባው ስካይ ላይት ሆቴል ተመረቀ
አዲስ አበባ ጥር 19/2011 የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ያስገነባው ስካይ ላይት ሆቴል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ተመርቋል።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የአፍሪካ ኀብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ታዋቂ ግለሰቦች ተገኝተዋል።
ለምረቃ የበቃው ስካይ ላይት ሆቴል 373 የመኝታ ክፍሎች ያሉት ነው።
ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የኢትዮጵያ ፣ የአውሮፓና የቻይና ሬስቶራንቶችም አሉት።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በተጨማሪም የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናልን የማስፋፊያ ፕሮጀክት መርቀዋል።
የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናሉ በዓመት 22 ሚሊዮን መንገደኞችን ማስተናገድ የሚችል ነው።