ቀጥታ፡

የቮሊቦል ውድድር በመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ

ጎባ ጥር 18/2011 የኢትዮጵያ ቮሊቦል ፌዴሬሽን ያዘጋጀውና ስምንት ክለቦች የሚሳተፉበት  የወንዶች የሀበሻ ሲምንቶ ፕሪሚየር ሊግ ስድስተኛ ሳምንት ጨዋታ ዛሬ በባሌ ሮቤ መዳ ወላቡ ስታዲዬም ተካሄደ።

በውድድሩ የመዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የቮሊቦል ክለብ ጣና - ባህርዳርን ሶስት ለአንድ  በሆነ ውጤት አሸነፏል ፡፡

በውድድሩ ስነስርዓት ወቅት የተገኙት የኢትዮጵያ ቮሊቦል ፌዴሬሽን ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተክሉ ሸዋዬ እንደገለጹት ፕሪሚየር ሊጉን መዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ አስር ነጥቦችን በመሰብሰብ ቀዳሚ ነው፡፡

ወላይታ ዲቻና ሙገር  በቅደም ተከተል  ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ ላይ ናቸው። 

የኢትዮጵያ የቮሊቦል ፌዴሬሽን የሀበሻ ስምንቶ ፕሪሚየር ሊግ ስምንት ቡድኖች የሚሳተፉበት መሆኑን  ኃላፊው አመለክተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም