አምባሳደር አብዱልፈታህ አብዱላሂ የሹመት ደብዳቤ ለኩዌት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቀረቡ - ኢዜአ አማርኛ
አምባሳደር አብዱልፈታህ አብዱላሂ የሹመት ደብዳቤ ለኩዌት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቀረቡ
አዲስ አበባ ጥር 16/2011 በኩዌት የኢትዮጵያ መንግስት ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር
አብዱልፈታህ አብዱላሂ የሹመት ደብዳቤያቸውን አቀረቡ።
አምባሳደሩ ባለፈው ቅዳሜ ታህሳስ 11 ቀን 2011 የሹመት ደብዳቤያቸውን ያስረከቡት ለኩዌት ተቀዳሚ ምክትል
ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ ሳበህ ካሊድ አልሳባህ ነው።
በዚሁ ወቅትም አምባሳደሩና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የሁለቱን አገራት ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ወደፊት በጋራ
በሚሰሩ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል።
አምባሳደሩ በኩዌት የሚኖራቸው ቆይታ የተሳካ እንዲሆን አስፈላጊውን ድጋፍ የሚያደርጉላቸው መሆኑን ተቀዳሚ
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አረጋግጠውላቸዋል።
ኢትዮጵያና ኩዌት ረዥም ጊዜ ያስቆጠረ ዲፕሎማሳያዊ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን ኩዌት በኢትዮጵያ የመሰረተ ልማት
ተሳትፎ መስኮች ድጋፍ አንደምታደርግ የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላከው
መግለጫ አመልክቷል።