እግር ኳስ ለሰላም እጦት ምክንያት ሊሆን አይገባም---የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን ፕሬዝዳንት - ኢዜአ አማርኛ
እግር ኳስ ለሰላም እጦት ምክንያት ሊሆን አይገባም---የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን ፕሬዝዳንት
መቀሌ ጥር 13/2011 " እግር ኳስ ለፍቅርና ለአንድነት እንጂ ለሰላም እጦት ምክንያት ሊሆን አይገባም ሲሉ " የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴረሽን ፕረዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ገለጹ።
ከሰባት ወራት በፊት በአዲስ አበባ ስታዲዮም የኢትዮጵያ ቡናና መቀሌ 70 እንደርታ እግር ኳስ ክለቦች ሲጫወቱ ደጋፊዎች በፈጠሩት ችግር ለደረሰው ጥፋት ዛሬ በመቀሌ ከተማ የይቅርታ ስነስርዓት ተኳሄዷል፡፡
በስነስርዓቱ ወቅት የተገኙት አቶ ኢሳያስ ጅራ ባስተላለፉት መልዕክት "የኢትዮጵያ ህዝብ በስነ ምግባሩ የታነፀ ኢትዮጵያዊነት የሚያስተምር ስፖርተኛ ይፈልጋል "ብለዋል።
የስፖርትን ልማት ለማጠናከር ሁሉም አመራር በቁርጠኝነት መስራት እንደሚጠበቅበት አመልክተው " እግር ኳስ ለፍቅርና ለአንድነት እንጂ ለሰላም እጦት ምክንያት ሊሆን አይገባም " ሲሉ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ቡና ክለብ ስራ አስኪያጅ አቶ ስንታየሁ በቀለ እና የመቀሌ 70 እንደርታ ክለብ ስራ አስኪያጅ አቶ ሽፈራው ተክለኃይማኖት በወቅቱ በተፈጠረው ችግር ይቅርታ በመባባል መልካም ግንኙነታቸውን ለማጠናከር የጋራ መግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡
ጥር 14 ቀን በትግራይ ዘመናዊ ስታዲዮም የኢትዮጵያ ቡና ከመቀሌ 70 እንደርታ ጋር የፕሪሜር ሊግ ውድድራቸውን የሚካሄዱ መሆናቸውን በዚሁ ስነስርዓት ወቅት ተገልጿል፡፡