ቀጥታ፡

በአፋር የአንጀት ጥገኛ ትላትል መከላከያ መድኃኒት እደላ ተጀመረ

ሰመራ ጥር 13/2011 በአፋር ክልል እድሜያቸው ከአምስት እስከ 14 ዓመት ለሆናቸው ህጻናት የአንጀት ጥገኛ ትላትል በሽታ መከላከያ መድኃኒት እደላ ተጀመረ ።

በክልሉ ሶስት ወረዳዎች ዛሬ በተጀመረው  የመድኃኒት እደላ 68ሺህ የሚሆኑ ህጻናት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ይጠበቃል።

የመድኃኒት እደላው እየተካሄደ ያለው በትምህርት ቤቶች ውስጥ መሆኑን በክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ  የበሽታ መከላከል ኬዝቲም አስተባባሪ ወይዘሮ ሞሚና አብደላ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ገልጸዋል፡፡

"የኢትዮጵያ ቤተሰብ ጤና በቅርቡ ባካሄደው የዳሰሳ ትናት የበሽታው ምልክቶች በታየባቸው ኤሌደአር፣ ገለአሎና ሀደለኤላ ወረዳዎች የመድኃኒት እደላው ተጀምሯል"ብለዋል ።

እሰከ ጥር 17 ቀን 2011ዓ.ም. ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የሚካሄድ ነው።

የአንጀት ጥገኛ ትላትል ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት በስፋት የሚከሰት የጤና ችግር መሆኑን አስተባባሪው አመልከተዋል።

"ንጽህናው ያልተጠበቀ ምግብ መመገብ፣ በግልና አካባቢ ንጽህና ጉድለትና በባዶ እግር መሄድ የበሽታው አምጭ ተሃዋሲን በቃላሉ ወደሆዳችንና አንጀታችን  በመግባት በሸታው እንዲከሰት የሚያደርጉ ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው" ብለዋል።

እንደ አስተባባሪዋ ገለጻ በሽታው የልጆችን አካላዊና አዕምሯዊ እድገት በማቀንጨር አምራችና ጤናማ እንዳይሆኑ ያደርጋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም