የጊዳቦ ግድብ የምረቃ ስነ-ስርዓት ለሌላ ጊዜ መተላለፉ ተነገረ

55

ሀዋሳ ጥር 13/2011 በነገው ዕለት ይካሄዳል ተብሎ የነበረው የጊዳቦ ግድብ የምረቃ ስነ-ስርዓት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን የደቡብ ክልል መስኖ ተቋማት ልማት ኤጀንሲ አስታወቀ።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክትር አቶ አሸናፊ ሽብሬ ለኢዜአ እንደገለጹት በደቡብና ኦሮሚያ ክልል ከ13 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት ታስቦ የተገነባው የጊዳቦ ግድብ የምረቃ ስነስርዓት ላልተወሰነ ጊዜ ተላልፏል።

ግድቡ በደቡብ ክልል 5 ሺህ ሄክታር እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል 8 ሺህ ሄክታር መሬት በመስኖ ለማልማት ታቅዶ እንደተገነባ ጠቁመዋል።

የግድቡ ምረቃ ጥር 14 ቀን 2011 ዓ.ም ይካሄዳል ተብሎ እንደነበር አስታውሰው በስነ-ስርዓቱ ላይ ይገኛሉ ተብለው የሚጠበቁ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በስራ ምክንያት መገኘት እንደማይችሉ በመገለጹ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲተላለፍ መወሰኑን አስረድተዋል።

የምርቃ ስነ- ስርዓቱ ወደፊት እንደሚገለጽ አቶ አሸናፊ ተናግረዋል።

ግድቡ በነገው እለት እንደሚመረቅ መገለፁን ኢዜአ ቀደም ሲል መዘገቡ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም