ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የቀድሞውን የአይቮሪ ኮስት መሪ ሎረን ባግቦ በነጻ እንዲለቀቁ ወሰነ

84

ጥር 8/2011 ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የቀድሞውን የአይቮሪ ኮስት መሪ ሎረን ባግቦ ከቀረበባቸው ክስ በነጻ እንዲለቀቁ ውሳኔ አስተላልፏል።


ፍርድ ቤቱ ሎርን ባግቦን በፈረንጆቹ 2010 የተካሄደውን አወዛጋቢ ምርጫ ተከትሎ 3 ሺህ ሰዎች በሞቱበትና 500 ሺህ ሰዎች በተፈናቀሉበት ግጭት በሰብዓዊ መብት ጥሰት ከስሷቸው ነበር።

የቀድሞ የሀገሪቱ መሪ በተቀናቃኛቸው አለሳኔ ኦታራ የተሸነፉበትን የምርጫ ውጤትአልቀበልም በማለታቸው ግጭት መከሰቱም ይታወቃል።

ባግቦ 2011 ላይ በቤተ መንግስታቸው ውስጥ እያሉ በተባበሩት መንግሥታትና በፈረንሳይ በሚደገፉት የፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል።

የቀድሞ የሀገር መሪ ሆኖ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተከስሰው የቀረቡ የመጀመሪያው ሰው ሎረን ባግቦ ናቸው።

ፍርድ ቤቱ በዋለው ችሎት ዓቃቤ ሕግ በሎረን ባግቦ ላይ ለቀረቡት የወንጀል ክስ በቂ ማስረጃዎችን ማቅረብ እንዳልቻለም ነው ያለው።

በመሆኑም የቀድሞው የአይቮሪ ኮስት መሪ በነጻ እንዲለቀቁ ሲል ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ሰጥቷል።

ምንጭ፦ቢቢሲ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም