አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ፍርድ ቤት ቀረቡ

70

አዲስ አበባ ጥር 7/2011 የአክሰስ ሪል ስቴትና የዘመን ባንክ መሥራች አቶ ኤርሚያስ አመልጋ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት

ቀረቡ።

አቶ ኤርሚያስ አመልጋ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት አርብ ጥር 3 ቀን 2011 ዓ.ም  ቢሆንም ጉዳያቸው በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ ወንጀል ችሎት የታየው ዛሬ ረፋዱ ላይ ነው።

አቶ ኤርሚያስ ፍርድ ቤት የቀረቡት ለብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) በሸጡት የቀድሞ ኢምፔሪያል ሆቴል ጋር በተገናኘ መሆኑ ታውቋል፡፡

አቶ ኤርሚያስ አመልጋ 51 ሚሊዮን ብር ግምት ያለውን ኢምፔሪያል ሆቴል በ75 ሚሊዮን ብር ለሜቴክ በመሸጥ፣ 24 ሚሊዮን ብር የሚገመት በመንግስት ላይ ጉዳት አድርሰዋል ተብለው መጠርጠራቸውን ነው ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ የገለፀው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም