የአፄ ቴዎድሮስ 200ኛ ዓመት ልደት በጎንደር ተከበረ

81

ጎንደር  ጥር 6/2011 የአፄ ቴዎድሮስ 200ኛ ዓመት የልደት በዓል በጎንደር ከተማ ተከበረ።

በከተማዋ ዋና ዋና ጎዳናዎች በተከበረው በዓል ላይ በንግሥና ዘመናቸው የተጠቀሙባቸው የጦር መሣሪያዎች ታይተዋል።

የአማራ ክልል ፖሊስ ማርሽ ባንድም ለበዓሉ ድምቀት ሰጥቷል፡፡

አርቲስት መሃሪ ደገፋው በክብረ-በዓሉ ባስተላለፈው መልዕክትም ''ጎንደር የአንዲት ኢትየጵያ ግንባታ መሠረት ጣይ በመሆኗ ይህንን ታሪኳን የሚያስቀጥል ትውልድ ባለቤት ልትሆን ይገባል'' ብሏል፡፡

ወጣት አንደበት የማታው በሰጠው አስተያየት አፄ ቴዎድሮስ ዘር፣ ቀለም እንዲሁም ሃይማኖትን መሠረት ሳያደርጉ ያስተላለፉለትን አገር ወጣቱም ፈለጋቸውን በመከተል ሊገነባት እንደሚገባ አመልክቷል፡፡

የክብረ በዓሉ አስተባባሪ ወጣት ዓለምሰገድ ይፍሩ በበኩሉ የከተማዋ ወጣቶች በጎንደርና አካባቢው የሚታየውን የሰላም መደፍረስን በማውገዝ ለሌሎች ተምሳሌት እንዲሆኑ ጠይቋል፡፡

አቶ ይርጋ ጌታሁን በበኩላቸው ወጣቱ ትውልድ የጎንደርን ሰላም በማይፈልጉ ኃይሎች አላማ ሰለባ ሳይሆን፤ የጥንት አባቶቻቸውን ፈለግ መከተል እንዳለባቸው አሳስበዋል።

''ታሪክን በማወቅ ሌላ አዲስ ታሪክ ለመስራት መንቀሳቀስ ይገባል'' ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም