በኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ምርጫ የተቃዋሚው እጩ ፌሊክስ ትሽሴኬዲ አሸነፉ

71

 አዲስ አባባ ጥር 2/2011 ከፍተኛ ፉክክር የታየበትን የዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ ምርጫ የተቃዋሚው እጩ ፌሊክስ ትሽኬዲ ማሸነፋቸውን የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ገልጿል።

ሌላኛው የተቃዋሚ ተወዳዳሪ ማርቲን ፋዩሉ ውጤቱ ተጭበርበሯል አንቀበለውም የሚል መግለጫ ሰጥተዋል።

በአሁኑ ወቅት ሀገሪቱን በማስተዳደር ላይ ያሉት ጆሴፍ ካቢላ ከ18 ዓመታት በኋላ ከስልጣን እንደሚወርዱ ይጠበቃል።

አሸናፊው ትሽሴኬዲ ኪኒሻሳ ውስጥ ለደጋፊዎቻቸው ባረጉት ንግግር የመላ ኮንጎአውያን ፕሬዚዳንት እሆናለሁ ብለዋል።

ትሽሴኬዲ ከ18 ሚሊየን መራጮች ውስጥ 38.57 በመቶ ድምፅ ማግኘታቸውን የምርጫ ኮሚሽነሩ ኮርኔል ንንጋ ተናግረዋል።

በምርጫው ትሽሴኬዲ 7 ሚሊየን፣ ፋዩሉ 6.4 ሚሊን እና በካቢላ የቀረቡት እጩ ኢማኑኤል ራምዛኒ ሻዳሪ 4.4 ሚሊየን ድምፅ ማግኘታቸውን የምርጫ ኮሚሽኑ ገልጿል።

ፊሊክስ ቲሽኬዲ በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንግሬሽን የተቃዋሚ መሪ የነበሩት ኢቲኔ ቲሽኬዲ ልጅ መሆናቸውም ተጠቁማል፡፡

በዚህም መሰረት ፊሊክስ ቲሽኬዲ ከተቃዋሚ ዕጩ ተወዳዳሪዎቹ ማርቲን ፊውሉ እና ከገዥው ፓርቲ ኢማኑዌል ሻዳሪን አሸንፈዋል፡፡

የትሽሴኬዲ አሸናፊነት በሚቀጥሉት 10 ቀናት በሕገመንሥታዊ ፍርድ ቤቱ ከተረጋገጠ እ.ኤ.አ በ1960 ሀገሪቱ ከቤልጀም ነጻነቷን ካገኘች በኋላ በምርጫ ስልጣን የተረከቡ የመጀመሪያው መሪ ይሆናሉ።


ምንጭ፦ቢቢሲ እና ሲጂቲኤን

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም