የአየርላንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር አክሱምን እየጎበኙ ነው

89

አክሱም ጥር 2/2011 የአየርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዮ ቫራድካር በኢትዮጵያ የጀመሩትን ጉብኝት በመቀጠል ዛሬ ከሰዓት በኋላ አክሱም ከተማ ገቡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክሱም አጼ ዮሀንስ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ  በትግራይ ክልል በምክትል ርእስ መስተዳድር መአረግ የከተማ ልማት ንግድና ኢንዱስቱሪ ቢሮ ሀላፊ ዶክተር አብረሀም ተከስተ አቀባበል አድርጎውላቸዋል፡፡

የሀይማኖት አባቶች፣የአገር ሽማግሌዎችና የአክሱም ከተማ ነዋሪዎች በተገኙበት አቀባበል ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ባህላዊ ልብስና የአክሱም ሀወልት ቅርጽ የያዘ የእደ ጥበብ ስራ ስጦታ ተበርክቶላቸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዮ ቫራድካር  በትግራይ ማእከላዊ ዞን ታህታይ ማይጨው ወረዳ በአይሪሽ ድጋፍ የተገነቡ የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን ጎብኝተዋል።

በወረዳው በአይሪሽ ፕሮጀክት ድጋፍ የተገነቡ አንድ ጤና ጣቢያ አንድ ክሊኒክ፣አንድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤትና የአርሶ አደሮች ማሰልጠኛ ማእከል መሆናቸውንም የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ አበበ ብርሀነ ገልጸዋል፡፡

የማብራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ለመገንባት የአየርላንድ መንግስት ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን አስተዳዳሪው ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በክልሉ ሰሜን ምእራብ ዞን በሚገኝ የኤርትራ ስደተኞች ማቆያ ጣቢያና በአይሪሽ ድጋፍ የተሰሩ የምግብ ዋስትና ፕሮጀክትን ነገ ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም