የጋምቢያ የእውነት አፈላላጊ ኮሚሽን በቀድሞ ስርአት የተፈፀሙትን በደሎች መስማት ጀመረ

74

የጋምቢያ የእውነት አፈላላጊ ኮሚሽን በቀድሞ ስርአት የተፈፀሙትን በደሎች መስማት ጀመረ

ታህሳስ 30/2011 የጋምቢያ የእውነት፣የአንድነትና የካሳ ኮሚሽን እኤአ በ1994 በጃሜህ ተመርቶ የሃገሪቱን የህገመንግስት ስርአት በወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት በማስወገድ ለ22 አመት የመራው ስርኣት ላይ ስለነበረው ሁኔታ የምስክሮችን ቃል መስማት ጀምሯል፡፡

የሃገሪቱ ዜጎች ሃገሪቱን ለ22 አመት ሲያስተዳድር የነበረው ስአርት ሲፈፅም የነበረውን በደል በማሰማት ፍትህ እየጠየቁ ነው፡፡


የሲጂቲን አፍሪካ ዘገባ እንደጠቆመው የጃምሄህ ስርአት ዜጎችን በማሰቃየት እና በመሰወር የሚከሰስ ሲሆን በመጨረሻም ከስልጣን እንዲወርድ ምክንያት ሆኗል፡፡ 


ኮሚሽኑ ለሁለት አመት የሚቆይ ሲሆን ጃሜህ በመፈንቅለ መንግስት ወደ ስልጣን የመጡበትን ሁኔታና ለሁለት አስርት አመታት ስልጣን ላይ እንዲቀዩ ሲሰሩ የነበሩ ግለሰቦችና ተቋማትን ሁኔታ ይመረምራል፡፡ 


“ሃገሪቱ ኮሚሽኑ ያስፈለጋት ያለፈውን ስህተት ላለመድገምና የትኛውም መንግሰት በጋምቢያ ላይ አምባገነናዊ ሰርአት እንዳይገነባ ነው “ ያሉት የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ላሚን ሲስ ናቸው፡፡ 

የሃገሪቱ ባለስልጣናት ያለፈውን ስህተት በማረም የሰብአዊ መብቶችና የሕግ የበላይነት የተረጋገጠባት ሃገር እንድትሆን እንደሚሰሩ መግለፃቸውን ዘገባው አስታውሷል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም