የ2019 አፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅ ሀገር ዛሬ ይታወቃል

79

ታህሳስ 30/2011 የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የ2019 የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅ ሀገር ዛሬ እንደሚለይ አስታውቋል፡፡

ካፍ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ 24 ብሄራዊ ቡድኖች የሚሳተፉበትን የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅ ሀገርን በነገው እለት እንደሚያሳውቅ ገልጾ የነበረ ቢሆንም ቀኑን ለምን ዛሬ እንዳደገረው የገለፀው ነገር የለም፡፡

ደቡብ አፍሪካ እና ግብጽ ውድድሩን ለማስተናገድ እስካሁን ለካፍ ይፋዊ ጥያቄ ያቀረቡ ሀገራት ናቸው፡፡

የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሽን ካሜሩንን የ2019 አፍሪካ ዋንጫ አስተናጋጅ አድርጎ የመረጠ ቢሆንም ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ውድድሩን ለማስተናገድ የሚያስችል በቂ ግዝጅት ባለማድረጓ ተቀምታለች፡፡

የጊኒ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በ2023 ሊያስተናግድ የነበረው አፍሪካ ዋንጫ ለሁለት አመት እንዲራዘም ከስምምነት ላይ ደርሷል፡፡

የውድድሩ አስተናጋጅ ተደርጎ በዛሬው እለት የሚመረጥ ሀገር በስድስት ወራት ውስጥ መዘጋጀት ይኖርበታል ተብሏል፡፡

የ2019 አፍሪካ ዋንጫ እኤአ ከሰኔ 15 እስከ ሀምሌ 13 ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የውድድሩ አዘጋጅ ሀገር በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር ይገለፃል፡፡
የአፍሪካ የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ሽልማትም የዛሬው ዝግጅት አንዱ አካል ሲሆን የግብፁ ሞሀመድ ሳላ በድጋሚ የማሸነፍ እድሉ ሰፊ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

ምንጭ፡ ቢቢሲ ስፖርት

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም