ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መንገዶች ባለስልጣንና ጠቅላይ አቃቤ ህግን ጎበኙ

87

አዲስ አበባ ታህሳስ 26/2011 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣንና የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ መስሪያ ቤቶችን ጎበኙ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንገዶች ባለስልጣን የ100 ቀናት የስራ እንቅስቃሴን ለውጥ ተመልክተዋል።

ባምቢስ አካባቢ በሚገኘው የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ መስሪያ ቤት በመገኘትም በቢሮው የተደረገውን የለውጥ ሂደት ቃኝተዋል።

የጉብኝቱ ዓላማ "የተጀመረው ለውጥ መሬት ላይ ማረፉን መመልከት ነው" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ሁለቱም ተቋማት ለለውጥ ሂደት ወሳኝ ሚና አላቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ "በጉብኝቱ ጥሩ ነገሮችን ተመልክተናል" ሲሉም ገልጸዋል።

በለውጡ ሂደት "ላይነኩ የተቋቋሙ የሚመስሉ ነገሮችን በመለወጥ ህዝብ ጥሩ አገልግሎትና መስተንግዶ ማግኘት የሚችልበት አጋጣሚ እየተፈጠረ መምጣቱን አይተናል" ብለዋል።

የተቋማትን የለውጥ ሂደት አንድም በሪፖርት በሌላ በኩል ደግሞ በአካል በመገኘት እንመለከታለን ነው ያሉት።

በመሆኑም ተቋማት በ100 ቀናት ያደረጓቸውን መሻሻሎች መጎብኘታቸውን እንደሚቀጥሉ ያረጋገጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝቱ በፌዴራልና በክልል ተቋማትም እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም