ዶክተር ኢያሱ መርሃፅድቅ አዲሱ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ፀሐፊ ሆነዋል

65

አዲስ አበባ ታህሳስ 25/2011 ዶክተር ኢያሱ መርሃፅድቅ አዲሱ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ፀሐፊ ሆነው ተሹመዋል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ ባደረገው ስብሰባ በአዲሱ የሪፎርም አደረጃጀት መሠረት ሁለት ሹመቶችን መስጠቱን ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።

በስብሰባው ፌዴሬሽኑ በአዲስ መልክ ባዘጋጀው የአደረጃጀት ሪፎርም ጥናት መሠረት የሰው ሃብት አደረጃጀት ምደባው በአዲስ መልክ በአስቸኳይ እንዲጠናቀቅ ውሳኔ ማስተላለፉን ገልጿል።

ይሄንኑ ተግባራዊ ለማድረግ ሁለት ሹመቶችን የሰጠ ሲሆን በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ፀሐፊነት ዶክተር ኢያሱ መርሃፅድቅን መሾሙን አመልክቷል።

ስራ አስፈጻሚው አቶ ሰለሞን ገብረሥላሴን በፌዴሬሽኑ ምክትል ዋና ፀሐፊነት እና በእግር ኳስ ልማት ኃላፊነት መመደቡንም ገልጿል።

አቶ ሰለሞን ገብረሥላሴ ዶክተር ኢያሱ ከመሾማቸው በፊት የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ዋና ጸሐፊ ሆነው አገልግለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም