ቀጥታ፡

ጅማ አባጅፋር በሜዳው ውጤት አልቀናውም

ጅማ ታህሳስ 22/2011 ጅማ ስታዲዮም  ዛሬ በተካሄደው ስምንተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጅማ አባጅፋር እና ወልዋል አድግራት ዜሮ ለዜሮ ተለያዩ፡፡

ወልዋሎ አድግራት በመከላከል ላይ ተመስረተ ጨዋታ ያደረግ ሲሆን ጅማ አባጅፋርም  ኳስን አደረጅቶ በመጫዋትና ወደ ጎል በመቅረብ ረገድ  ከፍተት ታይቶበታል፡፡

በሁለቱም ቡድኖች መካከል ምንም አይነት ሙከራ ሳያደርጉ የመጀመሪያውን ግማሽ የጨዋታ ጊዜ አብቅቷል፡፡

በሁለተኛው ግማሽ የጅማ አባጅፋር ወደጎል በተደጋጋሚ በመድረስ በኩል የተሻለ ቢሆንም  ውጤት አለቀናውም፡፡

በጅማ አባጅፋር በኩል በ34 ደቀቃ  ንጋቱ ገብረስላሴ በ85 ደቂቃ  ኤርሚያስ ኃይሉ የቢጫ ማስጠንቀቂያ ካርድ የተመለከቱ ሲሆን በወልዋሎ አድግራት በኩል በ11ኛው ደቂቃ አብዱልዓዚዝ ኬይታ እና  በ13 ደቂቃ አፈወርቅ ኃይሉ ቢጫ ካርድ አይተዋል፡፡

በ57 ደቂቃ  ደግሞ አስራት መገርሳ  በቀጥታ ቀይ ካርድ በመመለክቱ ምክንያት ከሜዳ  በመውጣቱ ወልዋሎ አድገራት በጎደሎ ቢሆን ተጫውተው ነጥብ ተጋርተው መውጣት ችለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም