በሳዑዲ አረቢያ ታስረው የቆዩ 451 ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ

129
አዲስ አበባ16/2011 በሳዑዲ አረቢያ ማረሚያ ቤት ውስጥ የታሰሩ 451 ዜጎች ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ማድረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር  አስታወቀ። ወደ አገራቸው የተመለሱት ዜጎች በጂዳ፣ በጂዛንና አካባቢዋ በተለያዩ ጉዳዮች ተከሰው በእስር ላይ የቆዩ እስረኞች እንደነበሩም የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በላከው የፕሬስ መግለጫ አስታውቋል። ዜጎቹ ወደ አገራቸው ሊመለሱ የቻሉት ጠንካራ የዲፕሎማሲ ስራ በመከናወኑ መሆኑንም ነው በመግለጫው የጠቆመው። ባለፈው ሳምንትም ወደ 2 ሺ 400 የሚሆኑ ዜጎችን ከሳዑዲ አረቢያ ፣ 231 ዜጎችን ደግሞ ከታንዛኒያ መመለሳቸውን ከቃል አቀባይ ጽህፈት ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም