ፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ መድረክ ስርዓትና ደንብ ላይ ውይይት አደረጉ - ኢዜአ አማርኛ
ፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ መድረክ ስርዓትና ደንብ ላይ ውይይት አደረጉ
አዲስ አበባታህሳስ 13/2011 በህጋዊ መንገድ በአገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ፖለቲካ ፓርቲዎች በቀጣይነት የሚያደርጉትን የጋራ የውይይት መድረክ በሚመለከት ስርዓትና ደንብ ላይ ውይይት አደረጉ። ውይይቱ በቀጣይ ፓርቲዎቹ የሚያደርጉት የፖሊሲ ክርክር መድረኮች እንዴት መመራት አለባቸው የሚለውን በጋራ ለመወሰን መሆኑ ተገልጿል። ረቂቅ ደንቡ በአጠቃላይ በ12 አንቀጾች የተዘጋጀ ሲሆን፤ ወደፊት በሚደረገው የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክር ለመገናኛ ብዙሃን ሙሉ ለሙሉ ክፍት መሆን እንደሌለበት የሚያመለክት አንቀጽ ተካቶበታል።
በዛሬው ውይይት በቀረበው የስርዓትና ደንብ ረቂቅ "ይህ ቢካተት፣ይህ ቢቀነስ" የሚሉ ሃሳቦች ከተሳታፊዎች ቀርበዋል። ህዝብ የፖለቲካ ፓርቲዎቹን ሀሳብ ተረድቶ 'የትኛው የተሻለ ነው?' ብሎ ለመለየት የሚያስችለው የግልጽነት አሰራር መፈጠር እንዳለበትም ተናግረዋል። በመደርኩ የተሳተፉት የፓርቲ አመራሮች መካከል ዶክተር አረጋይ በርሄ ባስተያየታቸው "ህዝብ ሊፈርድ ከፈለግን ለህዝብ ግልጽ መሆን አለብን ማነው ገንቢ ሃሳብ የሚያመጣ ፤ማነው አፍራሽ ሃሳብ የሚያመጣ ፤ ማነው ቁም ነገር የሚናገር ፤ ማነው ቁም ነገር የለሽ የሚናገር፤ የሚለውን ግልጽ ስንሆንና ህዝብ ሲሰማን ነው፤ ከህዝብም መማር እንችላለን፤ ችግሮቻችንን አይቶ ሲነቅፈን፤ ይሄ ፓርቲ ቁም ነገር የለውም ብሎ ሊመዝነን ይችላል፤ ስለዚህ ክፍት መሆን አለበት የሚለውን አቋም ነው የማንሸራሽረው" ብለዋል። ሁለት ሶስተኛ በሚባለው ብልጫ በዛሬይቱ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ እዚህ መድረክ ባለውም የፖለቲካ ሃይሎች ሁኔታ እጅግ በጣም አስቸጋሪ ነው፤ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ቢያንስ ቢያንስ ላለፉት 20 ዓመታት ከኢህአዴግ ጋር ባደረግናቸው ክርክሮችና ድርድሮች መጨረሻ ላይ ኢህአዴግ ይሄን ካርድ ይመዛል፤ በድምጽ ብልጫ እንወስን፤እሱ ደግሞ ሂሳቡን ሁል ጊዜ እየሰራ ነው የሚመጣው፤ እንዴት እንደሚመጣ ሁላችንም እናውቃለን፤ ስለዚህ ይሄ በጣም አደገኛ አንቀጽ ነው የሚል እምነት አለኝ ˝ያሉት ደግሞ ዶክተር መረራ ጉዲና ናቸው። በተነሱት ሃሳቦች ላይ ማጠቃለያ የሰጡት የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚዴቅሳ በበኩላቸው ረቂቁ ፖለቲካ ፓርቲዎቹ በተነሱት በርካታ ግብዓቶች ዳብሮ ለቀጣይ ውይይት እንደሚቀርብ ተናግረዋል። ውይይቱ በቀጣይ ወደ ፖሊሲ አጀንዳዎች ገብቶ እንደሚካሄድም ጠቁመዋል። የተነሱ ሃሳቦች የተካተቱበት የመጨረሻ ረቂቅ ላይ ጥር 1 ቀን 2011 ዓ.ም ላይ ውይይት እንደሚደረግም ተናግሯል።