በሆሳዕና ከተማ 10 ሽጉጦች ከ358 ጥይቶች ጋር በግለሰብ ሱቅ ውስጥ ተያዙ

49
ሆሳዕና ታህሳስ 11/2011 በሆሳዕና ከተማ በአንድ ግለሰብ ሱቅ ውስጥ 10 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጦች ከ358 ጥይቶች ጋር ተደብቀው መገኘታቸውን የሃዲያ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ። የመምሪያው አዛዥ ኮማንደር ደሳለኝ ሽጉጤ ለኢዜአ እንደገለፁት ፖሊስ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያውን ሊይዝ የቻለው ከህብረተሰቡ በተደረገ ጥቆማ አማካኝነት ነው። በከተማው ሴች ዱና ቀበሌ ከተያዘው የጦር መሳሪያ ጋር ባለ ሱቁን ጨምሮ እጃቸው አለበት በሚል የተጠረጠሩ አራት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋላቸውንም ኮማንደሩ ተናግረዋል፡፡ ህብረተሰቡ ላከናወነው ተግባር ያመሰገኑት ኮማንደር ደሳለኝ ሰላምን የሚያደፈርስና የሚያጠራጥር መሰል ድርጊት ሲያጋጥም ለፖሊስ መጠቆሙን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም