ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ሱዳን ካርቱም ገቡ

69
አዲስ አበበ  ታህሳስ 10/2011 ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን  ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ምሽት ሱዳን ካርቱም ገብተዋል። ካርቱም ሲደርሱም የሱዳን ምክትል ፕሬዚዳንት መሐመድ የሱፍ ኪብር ተቀብለዋቸዋል። የጉብኝቱ ዋነኛ ዓላማ  የአገራቱን የድንበር ጉዳዮች ጨምሮ በተለያዩ የሁለትዮች ግንኙነት ላይ ለመነጋገር ነው። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ በሱዳን ቆይታቸው ከሱዳን ፕሬዝዳንት ኡማር አሰን አልበሽርና ሌሎች የአገሪቱ ከፍተኛ ባለሰልጣናት ጋር ተገናኝተው ይመክራሉ። ኢትዮጵያና ሱዳን ጠንካራ የሚባል የፖለቲካ፣ የዲፕሎማሲና የምጣኔ ኃብት ግንኙነት አላቸው።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም