ፕሬዚዳንት ግርማ የመልካም ዜጋ ምሳሌነታቸውን አሳይተዋል-ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ - ኢዜአ አማርኛ
ፕሬዚዳንት ግርማ የመልካም ዜጋ ምሳሌነታቸውን አሳይተዋል-ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ
አዲስ አበባ ታህሳስ 10/2011 ''የቀድሞው ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ለአገራቸው የመልካም ዜጋ ምሳሌነታቸውን አሳይተዋል'' ሲሉ የአገሪቷ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ። ፕሬዚዳንቷ ይህን ያሉት ዛሬ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ህልፈትን ተከትሎ ዛሬ በሚሌኒየም አዳራሽ በተካሄደው የአስከሬን ሽኝት መርሃ-ግብር ላይ ነው። አቶ ግርማ ኢትዮጵያን በፕሬዚዳንትነት ባገለገሉባቸው 12 ዓመታት የኢትዮጵያን ጥሪ ተቀብለው አቅማቸው የፈቀደውን ሁሉ በማድረግ መልካምነታቸውን ያሳዩ መሆናቸውን ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ተናግረዋል። በተለይ በአካባቢ ጥበቃ ስራዎች፣ ድጋፍ የሚሹ ሰዎችን በመደገፍ ሰናይ ተግባር በመፈጸም የመልካም ዜጋ ምሳሌነታቸውን አሳይተዋል ብለዋል።
''ሰላምን ሰብከው ይቅርታና ምህረት ያላቸውን ዋጋ አስተምረዋል'' ያሉት ፕሬዚዳንቷ እነዚህ የአቶ ግርማ መልካም ተግባራት ''ለኛ ኩራት ለእርሳቸው ደግሞ የዘላለም መታሰቢያ ሆነው ከኛ ጋር ይኖራሉ'' ብለዋል። ''የቀድሞው ፕሬዚዳንት ስንሰናበታቸው ከእርሳቸው የተማርነውን የአገር ፍቅር፣ ቅንነት፣ በንጹህነትና በታማኝነት ማገልግልን፣ ምንም እንሁን ከየትም እንምጣ የአንድ አገር ልጆች መሆናችንን በማሰላሰል ሊሆን ይገባል'' ብለዋል። ከአቶ ግርማ ጋር ለመጨረሻ ጊዜ የተገናኙት ከ6 ሳምንታት በፊት በቤተመንግስት በተደረገ የእራት ግብዣ ላይ እንደነበር ያስታወሱት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ''አቅምና ጉልበት ቢከዳቸውም እዕምሯቸው፣ ለዛቸውና ጨዋታቸው የምናውቀው ነበር'' ብለዋል። ''ክቡር ፕሬዚዳንት ረጅሙን ጉዞ ጨርሰዋል። የእርሶ ከዚች ዓለም መለየት የሚዘጋው ትልቅ ቤተ-መጻህፍት ነው። ቤተ-መጻህፍት ነበሩና ከእንግዲ የሚገባዎትን እረፍት ይረፉ እግዚአብሄር በቀኙ ያኑሮት ባለውለታችን ኖት'' በማለት የቀድሞውን ፕሬዚዳንት በክብር ተሰናብተዋል። ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብና ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን ተመኝተዋል።