የተለያዩ ተቋማት በቀድሞ ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሐዘን እየገለፁ ነው

97
አዲስ አበባ ታህሳስ 8/2011 የተለያዩ ተቋማት በቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ሞት የተሰማቸውን ሐዘን እየገለፁ ነው። በዛሬው እለት ሀዘናቸውን ከገለፁት መካከል የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን፣ የዲያስፖራ ማህበር፣ የብረታ ብረት ኢንጅነሪግ ኮርፖሬሽን፣ የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚና የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ይገኙበታል። ተቋማቱ ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ከወጣትነት ዕድሜያቸው ጀምሮ በታማኝነትና በትጋት ለአገራቸው ዕድገት ሲሰሩ የቆዩ ሰው እንደነበሩ ገልፀዋል። አቶ ግርማ  ከወታደር እስከ ርዕስ ብሄርነት ድረስ አገራቸውንና ህዝባቸው በከፍተኛ ፍቅርና ስሜት አገልግለዋል ሲሉም ነው ተቋማቱ ሀዘናቸውን የገለፁት። አክለውም አቶ ግርማ ዘመናዊ የስራ አተገባበርና የአየር ንብረት ጥበቃን የህይወታቸው ጥሪ በማድረግ በህይወት ዘመናቸው የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ያበረከቱ መሪ እንደነበሩም አትተዋል። ተቋማቱ ለቀድሞ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ቤተሰቦችና ለኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናትን ተመኝተዋል። አቶ ግርማ ታህሳስ 19 ቀን 1917 ዓ.ም. በአዲስ አበባ የተወለዱ ሲሆን ላለፉት 12 ዓመታት የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንትነት ሆነው አገልግለዋል። የቀድሞ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ የቀበር ስነስርዓት ከነገ በስቲያ ረቡእ አዲስ አበባ ውስጥ ይፈፀማል። በእለቱም አስከሬናቸው ከጥዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በሚሌኒየም አዳራሽ ህዝባዊ ሽኝት ይደረግለታል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም